መራሔ ጽድቅ ሰንበት ትምህርት ቤት logoፍኖተ ሎዛ ቅድስት ማርያምመራሔ ጽድቅ

የፍኖተ ሎዛ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን

መራሔ ጽድቅ ሰንበት ትምህርት ቤት

ህፃናት እና አደጊ · ወጣት

ልጆችንና ወጣቶችን በኦርቶዶክሳዊ እምነት፣ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንና በመልካም ሥነ ምግባር አንጾ ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር የሚጠቅሙ ትውልድ ማፍራት።

ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም።
ምሳሌ 22፥6

ስለ እኛ

“መራሔ ጽድቅ” — ወደ ጽድቅ የሚመራ

መራሔ ጽድቅ ሰንበት ትምህርት ቤት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር፣ በአዲስ አበባ ብርጭቆ አካባቢ በሚገኘው የፍኖተ ሎዛ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተቋቋመ የሰንበት ትምህርት ቤት ነው።

ሰንበት ትምህርት ቤቱ በሁለት ክፍሎች ያገለግላል፤ ህፃናት እና አደጊ ከደቂቅ እስከ ስድስተኛ ክፍል፣ ወጣት ደግሞ ከሰባተኛ እስከ አሥራ አንደኛ ክፍል። እያንዳንዱ ክፍል የራሱ አገልጋዮችና መርሐ ግብር አለው፤ በአገልጋዮች መሪነት በየሳምንቱ ያስተምራል። ወላጆችም የልጆቻቸውን ዕድገት በቅርበት እንዲከታተሉ ከቤተሰብ ጋር አብሮ ይሠራል።

ህፃናት እና አደጊ · Hitsanat-Adagi

  • መደበኛ (በጋ)በትምህርት ዘመኑ በየሳምንቱ የሚሰጥ ትምህርት።
  • ክረምትትምህርት ቤት በሚዘጋበት የክረምት ወራት የሚሰጥ ልዩ መርሐ ግብር።

ወጣት · Wetat

  • የማታከሥራና ከትምህርት በኋላ የሚሰጥ የምሽት ትምህርት።
  • የቀንበቀን የሚሰጥ መደበኛ ትምህርት።
  • የርቀትበአካል መገኘት ለማይችሉ የሚሰጥ የርቀት ትምህርት።
ፍኖተ ሎዛ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ ብርጭቆ አካባቢ፣ አዲስ አበባ

ጦማር

አዳዲስ መንፈሳዊ ትምህርቶች

ሁሉንም ያንብቡ

የምንማረው

እምነትን፣ ሥርዓትንና ሥነ ምግባርን

ትምህርተ ሃይማኖት

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት መሠረቶች፣ መጽሐፍ ቅዱስና የቅዱሳን ታሪክ።

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን

ጸሎት፣ ጾም፣ በዓላትና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚጠበቅ ሥርዓት።

መዝሙር

ያሬዳዊ ዜማንና መዝሙራትን በአንድነት መዘመር።

ፊደልና ግእዝ

የቤተ ክርስቲያን ቋንቋና ንባብ መሠረታዊ ትምህርት።

ግብረ ገብ

ለወላጆች መታዘዝ፣ ፍቅር፣ ትሕትናና መልካም ሥነ ምግባር።

ክፍሎች

ከደቂቅ እስከ አሥራ አንደኛ ክፍል

ህፃናት እና አደጊ

ከ5–14 ዓመት

ልጆች ገና በልጅነታቸው ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲያውቁ፣ እምነታቸውን እንዲማሩና በአገልግሎት እንዲያድጉ ይማራሉ።

ደቂቅ ክፍል

ከ5–8 ዓመት

ትንንሽ ልጆች በመዝሙር፣ በታሪክና በጨዋታ መሠረታቸውን ይይዛሉ።

ከአንደኛ – ስድስተኛ ክፍል

ከ9–14 ዓመት

በየዓመቱ አንድ ክፍል እያለፉ ትምህርቱን በደረጃ ይቀጥላሉ፤ ፈተናና የውጤት መግለጫ አላቸው።

ወጣት

ከ15 ዓመት ጀምሮ

ስድስተኛ ክፍልን የጨረሱ ልጆች ከነሙሉ መረጃቸው ወደ ወጣት ክፍል ይሸጋገራሉ፤ ትምህርቱን በጥልቀት ይቀጥላሉ፣ በአገልግሎትም ይሳተፋሉ።

ከሰባተኛ – አሥራ አንደኛ ክፍል

ከ15–19 ዓመት

ወጣቶች በየዓመቱ አንድ ክፍል እያለፉ የሃይማኖት፣ የግእዝና የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ትምህርታቸውን ይቀጥላሉ።

ይህ መድረክ ለምን?

ለአገልጋዮች፣ ለተማሪዎችና ለወላጆች የተዘጋጀ የሰንበት ትምህርት ቤቱ የመረጃ መድረክ።

አቴንዳንስ

የየዕለቱ አቴንዳንስ በQR ኮድ ይመዘገባል፤ ወላጆችም ያያሉ።

ውጤትና ሰርተፊኬት

የፈተና ውጤት፣ ደረጃና የውጤት መግለጫ በአንድ ቦታ።

ለወላጆች

የልጆቻቸውን አቴንዳንስና ውጤት በስልካቸው ይከታተላሉ።

ለወላጆች፡ መለያ ለማግኘት ጥያቄ ይላኩ፤ የሰንበት ትምህርት ቤቱ አስተዳዳሪ ካጸደቀው በኋላ በስልክ ቁጥርዎ ይገባሉ።

ጥያቄ ይላኩ